And Again Advisory AND AGAINADVISORY
Services Free Zone & Mainland How it works Insights UAE Business News
Stage two · Structure & Pathwayደረጃ ሁለት · Structure & Pathway

Sixty minutes,
and the answer in writing.
ስድሳ ደቂቃ፣
መልሱም በጽሑፍ።

Free Zone or Mainland. Which jurisdiction, which licence, what it costs, how many visas, and where your bank application is likely to run into trouble. Delivered as a written report within two working days.Free Zone ወይስ Mainland። የትኛው ክልል፣ የትኛው ፈቃድ፣ ምን ያህል እንደሚያስወጣ፣ ስንት ቪዛ እንደሚፈቀድ፣ እና የባንክ ማመልከቻዎ የት ላይ ሊቸገር እንደሚችል ያካተተ፤ በሁለት የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ይደርስዎታል።

Book a Pathway Session · AED 500 →Pathway Session ይያዙ · AED 500 → Ask a question firstመጀመሪያ ጥያቄ ይጠይቁ Credited in full against your setup fee. You pick your time first; payment confirms the slot.ሙሉ በሙሉ ከማቋቋሚያ ክፍያዎ ተቀናሽ። መጀመሪያ ሰዓትዎን ይመርጣሉ፤ ክፍያው ቦታዎን ያረጋግጣል።
60
Minutes with a senior advisor, in English or Amharicደቂቃ ከከፍተኛ አማካሪ ጋር፣ በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ
2 days
Working days to your written Pathway Reportየሥራ ቀናት የጽሑፍ Pathway Report እስኪደርስ
6–8
Pages, with the verdict on page oneገጾች፣ ውሳኔው በገጽ አንድ ላይ
100%
Credited against your setup fee, or refundedከማቋቋሚያ ክፍያዎ ተቀናሽ፣ ወይም ተመላሽ
Watch firstመጀመሪያ ይመልከቱ

How Ethiopians set up a company in the UAE.ኢትዮጵያውያን በUAE ውስጥ ኩባንያ እንዴት ያቋቁማሉ።

Seven steps, in full, from our founder. Spoken in Amharic.ሰባቱም ደረጃዎች በሙሉ፣ ከመሥራቻችን። በአማርኛ።

Seven stepsሰባት ደረጃዎች And Again Advisory, in Amharic.And Again Advisory፣ በአማርኛ። Full 22 minutes on YouTubeሙሉውን 22 ደቂቃ በዩቲዩብ

The problemችግሩ

Free Zone or Mainland. The wrong answer costs you for years.Free Zone ወይስ Mainland። የተሳሳተው ምርጫ ለዓመታት ያስከፍልዎታል።

Most people start by asking what a licence costs. The first question is where your customers are. If you sell inside the UAE, a free zone licence does not allow that directly, and the quote you were sent will not mention it. And the licence is not the finish line: corporate bank accounts are where most new companies actually stall.አብዛኞቹ የሚጀምሩት ፈቃድ ስንት ያስወጣል ብለው በመጠየቅ ነው። የመጀመሪያው ጥያቄ ግን ደንበኞችዎ የት እንዳሉ ነው። በUAE ውስጥ የሚሸጡ ከሆነ Free Zone ፈቃድ ይህን በቀጥታ አይፈቅድልዎትም፣ የተላከልዎት የዋጋ ግምትም ይህን አይነግርዎትም። ፈቃዱም የመጨረሻው መስመር አይደለም፦ አብዛኞቹ አዳዲስ ኩባንያዎች የሚቆሙት በኩባንያ ባንክ ሒሳብ ላይ ነው።

01

Where you may sellየት መሸጥ እንደሚችሉ

Whether your activity is allowed to sell where you actually plan to sell.የሥራ ፈቃድዎ በእርግጥ ለመሸጥ ባቀዱበት ቦታ መሸጥ የሚፈቅድ መሆን አለመሆኑ።

02

Visa two, three, fourሁለተኛው፣ ሦስተኛው ቪዛ

The cost of the second, third and fourth visa, which is rarely the same as the first.የሁለተኛው፣ ሦስተኛውና አራተኛው ቪዛ ዋጋ። ከመጀመሪያው ጋር እኩል የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው።

03

The regulatorተቆጣጣሪው አካል

Whether your activity triggers a regulator, and what that adds to the sequence.የሥራ መስክዎ የተቆጣጣሪ ፈቃድ የሚያስፈልገው መሆኑ፣ እና ያ በሂደቱ ላይ የሚጨምረው ጊዜ።

04

The bank's questionየባንኩ ጥያቄ

What in your file a bank compliance officer will stop and question.በሰነድዎ ውስጥ የባንክ ተቆጣጣሪ ቆም ብሎ የሚጠይቅበት ነጥብ።

What you are paying forለምን እየከፈሉ ነው

Advisory, not a sales meeting.ምክክር እንጂ የሽያጭ ስብሰባ አይደለም።

A free consultation is a sales meeting, and everyone knows it. You get an hour of someone explaining why their zone is the right one, and you leave with a quote and no analysis. This is not that.ነጻ ምክክር የሽያጭ ስብሰባ ነው፣ ይህንንም ሁሉም ያውቀዋል። አንድ ሰዓት ሙሉ አንድ ሰው የእሱ ክልል ለምን ትክክለኛ እንደሆነ ያስረዳዎታል፣ እርስዎም የዋጋ ግምት ይዘው ያለ ትንተና ይወጣሉ። ይህ ግን ያ አይደለም።

01

Your activity, classifiedየሥራ መስክዎ በይፋዊ ምድብ

Translated into the official activity classification, with its code and any second or third activity the licence must carry.ወደ ይፋዊው የሥራ መስክ ምድብ ከነኮዱ ተተርጉሞ፣ ፈቃዱ መያዝ ከሚኖርበት ሁለተኛና ሦስተኛ የሥራ መስክ ጋር።

Pageገጽ 02
02

The jurisdiction verdictየክልል ውሳኔ

Free Zone or Mainland, with the reasoning. We name the option that lost and say why it lost.Free Zone ወይስ Mainland፣ ከምክንያቱ ጋር። ያልተመረጠውን አማራጭ በስም እንጠቅሳለን፣ ለምን እንዳልተመረጠም እንገልጻለን።

Pageገጽ 03
03

Cost, in five blocksወጪ፣ በአምስት ክፍሎች

Authority fees one-off and annual, premises, per-person immigration, and our fee. Fixed figures, never blended.የመንግሥት ክፍያ አንድ ጊዜና ዓመታዊ፣ ቢሮ፣ የኢሚግሬሽን ወጪ በአንድ ሰው፣ እና የእኛ ክፍያ። የተወሰነ ቁጥር፣ በፍጹም አይቀላቀልም።

Pageገጽ 04
04

Visas and peopleቪዛና ሰዎች

Allocation, per-person cost and sequence. We pay the medical and the Emirates ID on every visa, in every zone.ብዛት፣ የአንድ ሰው ወጪና ቅደም ተከተል። የሕክምና ምርመራና Emirates ID በእያንዳንዱ ቪዛ ላይ እኛ እንከፍላለን።

Pageገጽ 05
05

Banking readinessለባንክ ዝግጁነት

Your specific file, not banking in general. What works for you, what will be questioned, what to prepare.ስለ እርስዎ ሰነድ፣ ስለ ባንክ በአጠቃላይ አይደለም። የሚጠቅምዎት፣ የሚጠየቅብዎት፣ ማዘጋጀት ያለብዎት።

Pageገጽ 06

Why we charge · 1:35ለምን እንደምናስከፍል · 1:35 Thomas Gashaw Tadesse, founder.ቶማስ ጋሻው ታደሰ፣ መሥራች።

The termsውሉ

You should not be out of pocket for asking a straight question.ቀጥተኛ ጥያቄ ስለጠየቁ ብቻ ኪስዎ ሊጎዳ አይገባም።

01

Creditedተቀናሽ

The AED 500 comes off our service fee in full on any engagement signed within 90 days. If you go ahead with us, the session costs you nothing.በ90 ቀናት ውስጥ በሚፈረም ማንኛውም ውል ላይ AED 500 ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ክፍያችን ይቀነሳል። ከእኛ ጋር ከቀጠሉ፣ ምክክሩ ምንም አያስከፍልዎትም።

02

Refundedተመላሽ

If we conclude there is no viable UAE structure for what you want to do, we refund the AED 500 in full within five working days, and you keep the report.ለሚፈልጉት ሥራ በUAE ውስጥ አዋጭ መዋቅር የለም ብለን ከደመደምን፣ AED 500 በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይመለሳል፣ ሪፖርቱም የእርስዎ ይሆናል።

03

Yours either wayበሁለቱም መንገድ የእርስዎ

The only case where you are out of pocket is where we do the work, you take the report, and you go elsewhere. You would then have paid AED 500 for independent written analysis you can use anywhere.ኪስዎ ሊጎዳ የሚችለው እኛ ሠርተን፣ እርስዎ ሪፖርቱን ወስደው፣ ወደ ሌላ ቦታ ቢሄዱ ብቻ ነው። ያኔም በየትኛውም ቦታ የሚጠቀሙበትን ገለልተኛ ትንተና በAED 500 ገዝተዋል ማለት ነው።

Where this sitsይህ የት ላይ ነው

Stage two of five. The first one is still free.ከአምስቱ ደረጃ ሁለተኛው። የመጀመሪያው አሁንም ነጻ ነው።

The Pathway Session is the second stage, and it is the one where the decisions get made.The Pathway Session ሁለተኛው ደረጃ ነው፣ ውሳኔዎችም የሚወሰኑት በዚህ ላይ ነው።

01

Consultation

We learn your business and what matters most. Free and without obligation.ንግድዎንና ዋናውን ጉዳይ እንረዳለን። ነጻ እና ያለ ግዴታ።

Freeነጻ
02

Structure & pathway

Free Zone or Mainland, jurisdiction, and licence, with full cost clarity.Free Zone ወይስ Mainland፣ ክልል፣ እና ፈቃድ፣ ከሙሉ የወጪ ግልጽነት ጋር።

The Pathway Session · AED 500
03

Formation

Registration, trade name, licence, and documentation. Typically 7–14 days.ምዝገባ፣ የንግድ ስም፣ ፈቃድ፣ እና ሰነድ። በተለምዶ ከ7–14 ቀናት።

You get:ያገኛሉ፦ your licence issuedፈቃድዎ ተሰጥቶ
04

Activation

Visas, Emirates ID, corporate bank account, compliance, and workspace.ቪዛ፣ Emirates ID፣ የኩባንያ ባንክ ሒሳብ፣ ተገዢነት፣ እና የሥራ ቦታ።

You get:ያገኛሉ፦ an operational companyየሚሠራ ኩባንያ
05

Ongoing support

Renewals, new visas, and partner introductions as your business grows.ዕድሳት፣ አዳዲስ ቪዛዎች፣ እና ከአጋሮች ጋር ማስተዋወቅ።

You get:ያገኛሉ፦ deadlines handledቀነ ገደቦች ተያዘው

Most clients go from first conversation to a registered company in two to three weeks. Typical formation timeline is 7–14 business days from complete documentation.አብዛኞቹ ደንበኞች ከመጀመሪያው ውይይት እስከ ተመዘገበ ኩባንያ ከ2–3 ሳምንታት ይፈጅባቸዋል። ሰነዱ ከተሟላ በኋላ ምዝገባው በተለምዶ ከ7–14 የሥራ ቀናት ይወስዳል።

Fitለማን ይሆናል

Who this is for, and who it is not.ለማን ነው፣ ለማን ደግሞ አይደለም።

Book it ifይያዙት፣ ከሆነ

  • You have a specific activity in mind, not an idea you are exploring
  • You intend to move within the next 90 days
  • You have setup capital available, which in practice starts around AED 15,000
  • You are the person who decides, or you are deciding with a partner
  • You have been quoted by someone and want an independent read on it
  • ገና እያሰቡት ያለ ሐሳብ ሳይሆን የተወሰነ የሥራ መስክ ካለዎት
  • በሚቀጥሉት 90 ቀናት ውስጥ ሥራ ለመጀመር ካሰቡ
  • የማቋቋሚያ ካፒታል ካለዎት። በተግባር ከAED 15,000 አካባቢ ይጀምራል
  • ውሳኔ ሰጪው እርስዎ ከሆኑ፣ ወይም ከአጋርዎ ጋር እየወሰኑ ከሆነ
  • ከሌላ ሰው የዋጋ ግምት ደርሶዎት ገለልተኛ አስተያየት ከፈለጉ

Do not book it ifአይያዙት፣ ከሆነ

  • You are researching and have no decision to make yet
  • You are looking for a residence visa rather than a business
  • You want the cheapest possible licence and nothing else
  • You need a guaranteed approval or a guaranteed timeline. Nobody can give you that, and we will not pretend to.
  • ገና እያጠኑ ከሆነና ወደ ውሳኔ ደረጃ ገና ካልደረሱ
  • ንግድ ሳይሆን የመኖሪያ ቪዛ ብቻ እየፈለጉ ከሆነ
  • ከሁሉ የረከሰውን ፈቃድ ብቻ ከፈለጉ
  • የተረጋገጠ የፈቃድ መጽደቅ ወይም የተረጋገጠ የጊዜ ገደብ ከፈለጉ። ይህንን ማንም ሊሰጥዎት አይችልም፣ እኛም እንደምንችል አናስመስልም።
Questionsጥያቄዎች

The ones people actually ask.ሰዎች በእርግጥ የሚጠይቁት።

Everyone else offers a free consultation. Why do you charge?ሌሎቹ ሁሉ ነጻ ምክክር ይሰጣሉ። እናንተ ለምን ታስከፍላላችሁ?

They do. A free consultation is a sales meeting. You are paying for a written report you can take to your accountant, your bank or another advisor. It is yours whether you work with us or not, and because it is credited against the setup fee, if you go ahead the difference is zero.እውነት ነው፣ ይሰጣሉ። ነጻ ምክክር ግን የሽያጭ ስብሰባ ነው። እርስዎ እየከፈሉ ያሉት ወደ ሒሳብ ባለሙያዎ፣ ወደ ባንክዎ ወይም ወደ ሌላ አማካሪ ይዘው መሄድ ለሚችሉት የጽሑፍ ሪፖርት ነው። ከእኛ ጋር ቢሠሩም ባይሠሩም የእርስዎ ነው። ከማቋቋሚያ ክፍያው ስለሚቀነስም፣ ከቀጠሉ ልዩነቱ ዜሮ ነው።

Why should I pay before I know whether I want to work with you?ከእናንተ ጋር መሥራት እንደምፈልግ ሳላውቅ ለምን እከፍላለሁ?

That is the right question, and it is why the AED 500 is credited back. The only case where you are out of pocket is where we do the work, you get the report, and you decide to go elsewhere.ትክክለኛው ጥያቄ ይህ ነው። AED 500 ተመላሽ የሚደረግበትም ምክንያት ይኸው ነው። ኪስዎ ሊጎዳ የሚችለው እኛ ሠርተን፣ እርስዎ ሪፖርቱን ተቀብለው፣ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ቢወስኑ ብቻ ነው።

What if you tell me the UAE is not right for my business?UAE ለንግዴ አይስማማም ብትሉኝስ?

Then we refund the AED 500 in full within five working days, and you keep the report explaining why. It does not happen often. When it does, it is the most useful thing we can tell you.ያኔ AED 500 በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንመልሳለን፣ ምክንያቱን የሚያስረዳው ሪፖርትም የእርስዎ ይሆናል። ብዙ ጊዜ አይከሰትም። ሲከሰት ግን ልንነግርዎት ከምንችለው ሁሉ በጣም የሚጠቅምዎት ነው።

Can you just send me a quote instead?በምትኩ የዋጋ ግምት ብቻ መላክ አትችሉም?

We can send a number, but it would be a guess. The price depends on your activity, your visa count, whether you sell inside the UAE, and whether your activity needs a regulator. Change any one and the figure moves by thousands.ቁጥር መላክ እንችላለን፣ ግን ግምት ይሆናል። ዋጋው በሥራ መስክዎ፣ በቪዛ ብዛት፣ በUAE ውስጥ መሸጥ አለመሸጥዎ፣ እና የተቆጣጣሪ ፈቃድ ማስፈለጉ ላይ ይወሰናል። አንዱ ሲቀየር ቁጥሩ በሺዎች ይለወጣል።

Who runs the session?ምክክሩን የሚመራው ማነው?

Thomas Gashaw Tadesse, our founder and the manager named on our licence. And Again Advisory L.L.C-FZ is licensed in Meydan Free Zone, Dubai, licence 2542849.01. Sessions run in English or Amharic.ቶማስ ጋሻው ታደሰ፣ መሥራቻችንና በፈቃዳችን ላይ የተጠቀሰው ሥራ አስኪያጅ። And Again Advisory L.L.C-FZ በዱባይ Meydan Free Zone የተመዘገበ ሲሆን ፈቃዱ 2542849.01 ነው። ምክክሩ በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ ይካሄዳል።

When do I choose my session time?የስብሰባ ሰዓቴን መቼ ነው የምመርጠው?

First. You pick your slot on the calendar, and it is held for three hours while you confirm it with the AED 500 payment. Two sessions run each day and slots open up to eight days ahead. The invite, with the Google Meet link inside, arrives the moment you book.መጀመሪያ። ሰዓትዎን በቀን መቁጠሪያው ላይ ይመርጣሉ፣ በAED 500 ክፍያ እስኪያረጋግጡት ድረስም ለሦስት ሰዓታት ተይዞ ይቆያል። በቀን ሁለት ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፣ ሰዓቶችም እስከ ስምንት ቀናት ቀድመው ይከፈታሉ። የGoogle Meet ሊንክ የያዘው ግብዣ እንደያዙ ወዲያውኑ ይደርስዎታል።

Do you guarantee my licence or visa will be approved?ፈቃዴ ወይም ቪዛዬ እንደሚጸድቅ ዋስትና ትሰጣላችሁ?

No, and neither can anyone else. And Again Advisory coordinates with regulatory authorities and licensed partners. It does not issue licences, visas or approvals, and does not give legal or tax opinions. What we can do is make sure the file you submit is the right one, built correctly, in the right sequence.አንሰጥም፤ ሌላ ማንም ሊሰጥ አይችልም። And Again Advisory ከተቆጣጣሪ ባለሥልጣናትና ፈቃድ ካላቸው አጋሮች ጋር በማስተባበር ይሠራል። ፈቃድ፣ ቪዛ ወይም ማጽደቂያ አይሰጥም፤ የሕግ ወይም የግብር አስተያየትም አይሰጥም። እኛ ማድረግ የምንችለው የሚያቀርቡት ሰነድ ትክክለኛው መሆኑን፣ በአግባቡ መዘጋጀቱንና በትክክለኛው ቅደም ተከተል መሄዱን ማረጋገጥ ነው።

Start hereከዚህ ይጀምሩ

Let's map your pathway.መንገድዎን አብረን እንቀይስ።

Sixty minutes, a written verdict, and a number you can plan against. AED 500, credited in full against your setup fee. Refunded in full if there is no viable structure for your activity.ስድሳ ደቂቃ፣ የጽሑፍ ውሳኔ፣ እና ዕቅድ ሊያወጡበት የሚችሉት ቁጥር። AED 500፣ ሙሉ በሙሉ ከማቋቋሚያ ክፍያዎ ተቀናሽ። ለሥራዎ አዋጭ መዋቅር ከሌለ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ።

ንግድዎን በዱባይ ይጀምሩ። በአማርኛ እናገለግላለን።